ተጓዥ ኪነ-ጥበባት
5ኛው ተጓዥ ኪነ-ጥበባት መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ
- ግጥም
- ወግ
- መነባንብ
- ሙዚቃ
- ተውኔት እና ሌሎችም ተመድራኪ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን ይዞ ለኪነ-ጥበብ ስራ በእጅጉ አመቺ በሆነውና እስጢፋኖስ አካባቢ ግዮን ሆቴል ግቢ ውስጥ በሚገኘው ዉቡ ግሩቭ ጋርደን ቅዳሜ ነሀሴ 26/2015 ዓ.ም ይካሄዳል።
በዕለቱ አንጋፋና ወጣት ከያንያን
- ተወዳጆቹ ገጣሚዎች ሰለሞን ሳህለ፣ ምልእቲ ኪሮስ፣ እና ሰለሞን ሽፈራው
- ተወዳጁ የስምንተኛው ሺህ ተዋናይ ሱራፌል ብስራት፣ ጋዜጠኛ እና ተዋናይት ቤተልሄም አዳሙ
- እንዲሁም በቲክቶክና ሌሎች ሶሻል ሚዲያ ይበልጥ የሚታወቀው እጅግ ተወዳጅ የሆነው ኮሜዲያን ማሜ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
በዘፈን
- ጥለት ህብረ- ዜማ
- ድምጻዊት እድላዊት ሉሉ
- ድምጻዊ ትንቢተ ዮሃንስ
- ድምጻዊ አክሊል መለስ እንዲሁም የሃረሪው ተወዳጅ ድምጻዊ ዊሳም ኢህሳን በዘፈን ያስደስቱናል።
በመድረኩ እንደተለመደው አዳዲስና ወጣት ከያኒያንን ያስተዋውቀናል።
የተዋጣላቸው ከያንያንን ስራዎች ለመታደም ፣ የአዳዲስ ስራዎችን እና ሃሳቦችን የሚያሳዩ ን የነገ የኪነ-ጥበብ ሰዎችን ከወዲሁ ለመተዋወቅ
ቅዳሜ በግሩቭ ጋርደን እንገናኝ።
ለበለጠ መረጃ : 0975108685 ይደውሉ!!
Share This Event