
Trip to Awash Park & Doho Lodge
ውድ የጎጆ ሀይኪንግ ቤተሰቦች የአመቱን የመጨረሻ የአዳር ጉዞ ሰኔ 18-19 ከአዲስ አበባ 265 ኪ.ሜ ላይ ወደሚገኘው አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ እና ዶሆ ሎጅ የምናደርገውን ጉዞ ዳጉ በሚል ሰይመነው እንጓዛለን፡፡በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በሚኖረን ቆይታ በአዋሽ ወንዝ ፏፏቴ ግርማ እየተደመምን ፣ አዞን ፈራ ተባ እያልን እየጎበኘን ፣ በተፈጥሮ ፍል ውሀ ዋና ራሳችን እያደስን ፣ በፓርክ ውስጥ የእግር ጉዞ እያደረግን ከብርቅዬ አእዋፋት እና እንስሳት ጋር እየተጫወትን ፣ ምሽቱን በእሳት ዳር ጫወታ እያሸገንን የማይረሳ ጊዜን ለማሳለፍ ተዘጋጅተናል።
ቀን: ሰኔ 18
መነሻ ሰዓት: ማለዳ 12:30
መነሻ ቦታ: ሜክሲኮ ሸበሌ ሆቴል እንነሳለን
ዋጋ:
- 3200 ብር
-
ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ 100$ ይከፍላሉ
ክፍያ የሚያጠቃልለው:
- ቁርስ 1ቀን
- ምሳ 2 ቀን
- እራት
- ማደሪያ ቴንት
- የአስጎብኚዎች ክፍያ
- የመግቢያ ክፍያ
- የስካውት ክፍያ
- የደርሶ መልስ ትራንስፖርትን ያካተተ ነው።
ለበለጠ መረጃ:
- 0977772677
- telegram – t.me/gojohiking
- Facebook – fb.me/gojohiking
- Instagram- www.instagram.com/gojohiking
Share This Event